62 ሰዎችን አሳፍሮ ወደ ደሴ ይጓዝ የነበረ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ የእሳት ቃጠሎ አደጋ አጋጠመው።

589

ባሕር ዳር: የካቲት 11/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ 62 ሰዎችን አሳፍሮ ይጓዝ የነበረ አንድ ሀገር አቋራጭ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶብስ የእሳት ቃጠሎ አደጋ እንዳጋጠመው በአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅሕፈት ቤት አስታውቋል።
የእሳት ቃጠሎው የንብረት ውድመት ቢያደርስም በሰው ህይወት ላይ ምንም አይነት ጉዳት አለመድረሱ ተገልጿል።
አውቶብሱ አደጋው ዛሬ ረፋድ ላይ ያጋጠመው በዞኑ ጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ጎዳ ቀበሌ ሲደርስ መሆኑን በጽሕፈት ቤቱ የመንገድ ደኅንነትና ትራፊክ ክፍል ባለሙያ ዋና ሳጅን ወንድወሰን ጌታሁን ተናግረዋል፡፡
በደረሰው አደጋ ወሎ ዩኒቨርሲቲ ለመመዝገብ ተሳፍረው ይጓዙ የነበሩ ተማሪዎችን ሻንጣና ዶክመንት ጨምሮ የሌሎችን ተሳፋሪዎች ንብረትም ሙሉ በሙሉ ከአውቶቡሱ ጋር መውደሙንም ገልጸዋል።
አውቶብሱ የእሳት ቃጠሎ አደጋ ያጋጠመው በሞተሩ ላይ በተከሰተ የቴክኒክ ችግር እንደሚሆን ጠቅሰው፣ የቃጠሎው መንስዔ ለማጣራት ሙሉ የምርመራ ስራ መጀመሩን አስረድተዋል።
ተሽከርካሪው ከሽዋ ሮቢት ጀምሮ የጭስ ምልክት ያሳይ እንደነበርና አሽከርካሪው ‘‘ፍሬን ሸራ ነው’’ በሚል ሲያሽከረክር እንደነበር ከተሳፋሪዎች መረጃ መገኘቱንም አመልክተው፣ አሽከርካሪውና ረዳቱ በቁጥጥር ስር ውለው የማጣራት ስራ እየተካሄደ መሆኑም ታውቋል።
በተሽከርካሪው ውስጥ የነበሩ ተሳፋሪዎችም በሌላ መኪና ወደ ደሴ መላካቸውን አመልክተዋል፡፡
አሽከርካሪዎች የተሽከርካሪውን አካል በመፈተሽ የተሳፋሪውን ደህንነት የመጠበቅ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባቸውም ማስገንዘባቸውን ኢዜአ ዘግቧል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/