500 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞችን በቅርቡ ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መኾኑ ተገለፀ።

130

ሰኔ 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በታንዛኒያ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሽብሩ ማሞ በታንዛኒያ የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት(IOM) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቃሲም ሱፊና የድርጅታቸው የሥራ ኃላፊዎች ጋር በሀገሪቱ ስለሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ጉዳይ ሰፊ ውይይት አድርገዋል።
አምባሳደር ሽብሩ በታንዛኒያ በተለያዩ እስር ቤቶች ታስረው የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን ያሉበትን ሁኔታና ከእስረኞቹ በተለያዩ ጊዜያት እንደ ችግር የተነሱ ጥያቄዎችን ለድርጅቱ (IOM) ዋና ዳይሬክተር ለዶክተር ቃሲም በስፋት አብራርተዋል።
በውይይታቸው ወቅትም የእስር ጊዜያቸውን ያጠናቀቁትን ዜጎች ወደ አገር ቤት ለመመለስ የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የዓለም አቀፉን የስደተኞች ድርጅት ድጋፍ አስፈላጊ እንደኾነ አንስተዋል።
ዜጎች በእስር ቤት ቆያታቸው ሰብዓዊ መብታቸው መጠበቅ እንዳለበት በመጥቀስ በድርጅታቸው በኩል አስፈላጊው ሰብዓዊ እንክብካቤ ሊደረግላቸው እንደምገባም አምባሳደር አሳስበዋል።
አምባሳደር ሽብሩ ማሞ የIOM ድርጅት ለኢትዮጵያዊያን ስደተኞች እያደረገ ያለውን ሰብአዊ ድጋፍ አጠናክሮ መቀጠል እንዳለበት የጠየቁ ሲሆን እስከአሁን ለዜጎች ለተደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል::
የዓለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት(IOM) ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቃሲም ሱፊ በበኩላቸው ኢትዮጵያዊያንን ጨምሮ የብዙ ሀገር ዜጎች በህገ ወጥ መንገድ ወደ ታንዛኒያ ሀገር ገብተው በሀገሩ ፖሊስ ቁጥጥር ስር ውለው በተለያዩ እስር ቤቶች እንደሚገኙ ተናግረዋል።

በአሁኑ አስቸኳይ ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን 500 ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች በቅርቡ ከታንዛኒያ ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ዝግጅት እየተጠናቀቀ መኾኑን በመጥቀስ የተቀሩትን ዜጎች ከተለያዩ የዓለም አቀፍ ሰብአዊ ድርጅቶች ፈንድ በማፈላለግ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱበት ሁኔታ እንደሚመቻች በውይይታቸው ወቅት አብራርተዋል።
ክቡር ዶክተር ቃሲም ድርጅታቸው IOM በእስር ላይ ለሚገኙ ዜጎች አስፈላጊ ቁሳቁሶች ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥልና በእስር ቤት ቆይታቸው ወቅትም ሰብአዊ እንክብካቤ እንዲደረግላቸው ከሚመለከታቸው የታንዛኒያ የሥራ ኃላፊዎች ጋር በቀጣይ እንደሚነጋገሩ ገልጸዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/