5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡

0
199
5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ያካሂዳል፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) የኢፌዴሪ 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 8ኛ መደበኛ ስብሰባውን ዛሬ ያካሂዳል።
በስብሰባው የውጭ ግንኙነት እና የሰላም ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ እና የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴዎች ምክር ቤቱ ታህሳስ 15 ቀን 2013 ዓ.ም በቤኒሻንጉል ጉሙዝ በመተከል ዞን እና በሌሎች የሃገሪቱ አካባቢዎች የተፈጸመውን ግድያ አስመልክቶ ከተወያየ በኋላ በሰጠው አቅጣጫ መሰረት ያቀረቡትን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ የውሳኔ ሀሳቡን ያጸድቃል።
የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌደራል የዳኝነት አስተዳደር ለመወሰን የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል ተብሎ ይጠበቃል።
የህግ፣ ፍትህና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ረቂቅ አዋጅን በተመለከተ ያቀረበውን ሪፖርትና የውሳኔ ሃሳብ መርምሮ አዋጁን ያጸድቃል።
የኢትዮዽያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የካፒታል ገበያ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በኡጋንዳ መካከል የተደረገውን በወንጀል የሚፈለጉ ሰዎችን አሳልፎ የመስጠት ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።
በተጨማሪም በኢትዮጵያ መንግስት እና በኡጋንዳ መካከል የተደረገውን በወንጀል ጉዳዮች የጋራ የፍትሕ ትብብር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል ተብሎም ነው የሚጠበቀው።
በኢትዮጵያ መንግስት እና በደቡብ አፍሪካ መንግስት መካከል የዲፕሎማቲክ ወይም ሰርቪስ ፓስፖርት ለያዙ ሰዎች ቪዛን ለማስቀረት የተደረገውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ ይመራል።
እንዲሁም በኢትዮጵያ መንግስት እና በዓለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል የገጠር ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ መምራት፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የፖለቲካ ፖርቲዎች ምዝገባ እና የምርጫ ስነ-ምግባር አዋጅ ቁጥር 1162/2011 አንቀጽ 32(2)ን በጊዜያዊነት ስለማገድ ያቀረበውን ማሻሻያ መርምሮ ለሚመለከተው ቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ፋብኮ ነው የዘገበው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here