5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡

0
29

5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 16ኛ መደበኛ ስብሰባ ነገ ይካሄዳል፡፡

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ምክር ቤቱ ነገ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 16ኛ መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል ዋና ኦዲተር የሚያቀርበውን የፌዴራል መሥሪያ ቤቶች የ2012 በጀት ዓመት ሂሳብ የፋይናንስና ሕጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርት ያዳምጣል፡፡

በተጨማሪም ምክር ቤቱ ሁለት የትብብር ሥምምነት ረቂቅ አዋጆች ላይ ተወያይቶ ያጸድቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከምክር ቤቱ የማኅበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘ መረጃ ያመላክታል፡፡

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here