በኮሮናቫይረስ የተራዘመው ማራቶን ዛሬ እየተካሄደ ነው፡፡ የሴቶቸ ውድድር በኬንያውያን የበላይነት ተጠናቅቋል፤ የወንዶች ውድድር ገና በመካሄድ ላይ ነው፡፡
በ40ኛው የለንደን ማራቶን አንደኛ በመሆን ያሸነፈችው ኬንያዊዋ ብሪጌ ኮስጌ ስትሆን የገባችበት ሰዓት ደግሞ 2:18፡58 ነው፡፡ አሜሪካዊቷ ሳራ ሆል በ2፡22፡01 በመግባት ሁለተኛ ስትሆን ኬንያዊቷ ሩት ቼፒንጌቲች 2፡22፡05 በመግበባት ሦስተኛ መውጣት ችለዋል፡፡
ኢትዮጵያውያኑ አሸቴ በከሪ 2:22.51 4ተኛ እና መገርቱ ዓለሙ 2:24.23 በመግባት አምስተኛ ሆነዋል፡፡
በግርማ ተጫነ