35ኛው የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ ከሳምንት በኋላ በአዲስ አበባ እንደሚካሄድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ገለጸ።

0
113

አዲስ አበባ: ጥር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) 35ኛው አፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባዔ በሕብረቱ መቀጫ አዲስ አበባ ከሳምንት በኋላ ይካሄዳል ያለው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይህ ጉባዔ በሀገሪቱ እንዳይካሄድና ሀገሪቱንም በርካታ ችግሮች ውስጥ እንዳለች ለማስመሰል በርካታ የስውር ሴራዎች ሲሠሩ እንደነበር ገልጿል።

ኾኖም እንደ ሀገር ያለንበትን ሁኔታ በማስረዳትና ጉባኤውን ለማካሄድ ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ለማስረዳት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል ብለዋል የሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ቃል ዐቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ።

የአፍሪካ ሕብረት የመሪዎች ጉባኤ በግብርናና አልሚ ምግቦች ላይ ትኩረት አድርጎ ይወያያል ተብሏል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከካናዳው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋርም ስኬታማ ውይይት ማድረጋቸው የሳምንቱ የዲፕሎማሲ ተግባር ነበር ብለዋል።

ሌላው በሳምንታዊ መግለጫው የተነሳው የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቋም ትክክል እንዳልሆነና በኢትዮጵያ ላይ ያላቸውን የተሳሳተ አቋም እንዲያስተካክሉና ለአጥፊ ቡድኖች ያልተገቡ ድገፎችን እያደረጉ በመሆናቸው ይህን አቋማቸውን እንዲያርሙ ደብዳቤ ተጽፎ ተልኳል ነው ያሉት።

ዘጋቢ:- እንዳልካቸው አባቡ -ከአዲስ አበባ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/