20ኛው የባሕል ስፖርቶች ውድድር 16ኛው የባሕል ፌስቲቫል በአማራ ክልል አሸናፊነት ተጠናቀቀ።

24
ባሕር ዳር:መጋቢት 03/2015 ዓ.ም (አሚኮ)20ኛው የባሕል ስፖርቶች ውድድር መጋቢት 2/2015 ዓ.ም ፍጻሜውን አግኝቷል።
20ኛ የባሕል ስፖርቶች ውድድር እና 16ኛው የባሕል ፌስቲቫል በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል አስተናጋጅነት በቤንች ሸካ ዞን በሚዛን አማን ከተማ ከየካቲት 26/2015 ዓ.ም ጀምሮ በ11 ባሕላዊ ስፖርቶች ተካሂዷል።
የአማራ ክልል ባሕል ስፖርት ልዑካን ቡድን ከፍተኛ ፉክክር በማድረግ 20ኛውን የባሕል ስፖርቶች ውድድር እና 16ኛውን የባሕል ፌስቲቫል በፍጹም የበላይነት አጠናቋል።
20ኛ የባሕል ስፖርቶች ውድድር እና 16ኛው የባሕል ፌስቲቫል የሽልማት ሥነ-ስርዓት ዛሬ ይካሄዳል። መረጃው የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!