❝የኢትዮጵያን ሕልውና ለማስጠበቅ ቆርጠን ተነስተናል❞ ለመከላከያ ሠራዊት የተመዘገቡ የሁመራ ከተማ ወጣቶች

0
80

ሁመራ፡ መስከረም 06/2014 (አሚኮ) ኢትዮጵያ ያጋጠማትን የህልውና ፈተና ለመቀልበስና ለሀገራቸው ዘብ ለመቆም ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን እየተቀላቀሉ ይገኛሉ።

በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን በሁመራ ከተማ የሚኖሩ ወጣቶችም የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ተመዝግበዋል።

ወጣት ወንድም ድረስ እና ምስጋናው እንየው ለዘመናት ነፃነቷን አስከብራ የኖረችን ሀገር ክብሯን የደፈረውን አሸባሪ ቡድን ለመደምሰስ ቆርጠው መነሳታቸውን ገልጸዋል።

የመከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል ሲመዘገብ ያገኘነው ወጣት አስምሮ ገዳሙ ❝መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል ለሀገሬ ሉዓላዊነት ደምና አጥንቴን እገብራለሁ❞ ብሏል፡፡

ሌላኛው ወጣት እንደሻው አመኑ ለሀገሩ ያለውን ፍቅር በተግባር ለማሳየት እንደተመዘገበ ገልጾ የአማራ ወጣት መከላከያ ሠራዊትን በመቀላቀል ሀገሩን ለማዳን የበኩሉን እንዲወጣ ጠይቋል።

❝የኢትዮጵያን ሕልውና ለማስጠበቅ ቆርጠን ተነስተናል❞ ነው ያለው።

የሁመራ ከተማ ሰላምና ደኀንነት ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሻንበል ፍስሃ ቸሬ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል በከፍተኛ ደረጃ እየተመዘገቡ እና በንቃት እየተሳተፉ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

መከላከያ ሠራዊቱን ለመቀላቀል ለተመዘገቡ ወጣቶች ከተማ አስተዳደሩ ሽኝት ማድረጉንም ተናግረዋል።

ዘጋቢ፡- ያየህ ፈንቴ – ከሁመራ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m