❝የኢትዮጵያን ህልውና ለማስከበር የሀገር ዋልታና መከታ የሆነውን መከላከያ ሠራዊት ተቀላቅለናል❞ መከላከያ ሠራዊትን ለመቀላቀል የተሸኙ ወጣቶች

0
122

ገንዳ ውኃ: መስከረም 09/2014 ዓ.ም(አሚኮ) አሸባሪውና ወራሪውን ትህነግ በመደምሰስ የኢትዮጵያን ህልውና እንደሚያረጋግጡ በምዕራብ ጎንደር ዞን የመከላከያ ሠራዊትን የሚቀላቀሉ ወጣቶች ተናግረዋል።

የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን እና የሱ ተቀጽላና ተላላኪ የጥፋት ቡድንን በመደምሰስ የኢትዮጵያን ህልውና ለማስከበር የሀገር ዋልታና መከታ የሆነውን የመከላከያ ሠራዊት ለመቀላቀል መወሰናቸውንም ወጣቶች ገልጸዋል።

የታሪክ፣ የዘመንና የትውልድ ተወቃሽ ላለመሆን የህይወት መስዋትነት ከፍለው የኢትዮጵያን ሰላም እንደሚያረጋግጡ ነው ወጣቶቹ የተናገሩት።

የመከላከያ ሠራዊትን ለሚቀላቀሉ ወጣቶች በገንዳ ውኃ ከተማ ሽኝት ተደረጎላቸዋል።

የዞኑ የመከላከያ ምልመላ ዋና አስተባባሪ አቶ ዮናስ ጋዲሳ የሽብርተኛው ትህነግ ወራሪ ቡድን በምዕራብ ጎንደር ዞን ጦርነት ቢከፍትም አይቀጡ ቅጣት እንዲቀጣ በማድረግ በኩል የዞኑ ወጣቶች ከጸጥታ ኃይሉ ጋር በመቀናጀት ጀብድ ፈጽመዋል ብለዋል፡፡

ዛሬም የመከላከያ ሠራዊትን ተቀላቅለው ጠላትን ለመፋለም በወኔና በጀግንነት ታጥቀው ተነስተዋል ብለዋል።

ዘጋቢ፡- ቴዎድሮስ ደሴ – ከገንዳ ውኃ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m