❝የሸዋ ተራራዎች የሽብር ኃይሉ መፈንጫ ሳይሆኑ መቀበሪያ ናቸው❞ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ ንጉሡ ጥላሁን

0
161
ሕዳር 14/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ሀገር ለማፍረስ እያደረገ ያለዉን እንቅስቃሴ ለመግታት የሸዋ ሕዝብ ከፍተኛ ጀብዱ በመፈጸም አሸባሪውን ኀይል በገባበት እያሳደደ እየቀበረው እንደኾነ የሥራና ክህሎት ሚኒስትር ዲኤታ ንጉሡ ጥላሁን ተናግረዋል፡፡
❝የሸዋ ተራራዎችና ሸለቆዎች የሽብር ኃይሉ መፈንጫ ሳይሆኑ መቀበሪያቸዉ ይሆናሉ” ነው ያሉት፡፡
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል በ1982 በሸዋ ምድር የገጠመው ጠንካራ በትር ዛሬም አለ ያሉት አቶ ንጉሡ የሸዋ ሕዝብ ጠላቱን እንዴት መቅጣት እንዳለበት ያውቅበታል ብለዋል፡፡
ሊያጠፋ የመጣውን ጠላት አሁን በተጀመረው ጠንካራ አደረጃጀት በገባባቸዉ ቦታዎች ሁሉ በማሳደድ መቅበር እንደሚገባም ነው ያስረዱት፡፡
ቀዬን ሳይለቁ ትኩረትን ጠላት መምታት ላይ ማድረግ እንደሚገባም አስረድተዋል፡፡
አሁን ያለዉ አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ኀይል ተበታትኖ የእዉር ድንብር ጉዞ እያደረገ መሆኑን ያስረዱት ሚኒስትር ዲኤታዉ ሁሉም በነቂስ በመውጣት ወደ ፊት እንጅ ወደኋላ ላይመለስ በመትመም ጠላት በገባበት እንዳይወጣ ማድረግ እንደሚያስፈልግም ነው ያሳሰቡት፡፡
ዘጋቢ፡- ኤልያስ ፈጠነ
ተነሳ!!
መሪህን ተከተል!!
ሀገርህን አድን!!
ነፃነትህን አትስጥ !!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ