❝የመከላከያ ሠራዊት ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፤ማከማቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ ነው❞ የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ

0
249
ጥቅምት 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) መከላከያ ሠራዊት ያካሄዳቸው የአየር ድብደባዎችን በተመለከተ የተዛባ ግንዛቤ ቢኖርም፣ በተቃራኒው ጥቃቶቹ ዒላማ ያደረጉት የህወሓት የጦር መሣሪያ ማምረቻ ፤ማከማቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያዎችን ብቻ መሆኑን ነው የኢትዮጵያ ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ።
የመከላከያ ሠራዊት የሚያከናውናቸው እነዚህ ሥራዎች የሽብር ድርጅቱ ከባድ የጦር መሣሪያዎችን እና ሌሎች ሕገወጥ የጦር መሣሪያዎችን ለመሸሸግ የሚጠቀምባቸውን እና ወደ ወታደራዊ መገልገያነት የቀየራቸውን የተወሰኑ ቦታዎች ከጥቅም ውጭ ለማድረግ ያለመ ነው ብሏል።
በተለይም የሽብር ቡድኑ የመስፍን ኢንዱስትሪያል ኢንጂነሪንግ ኩባንያን የከባድ የጦር መሳሪያ ማከማቻ ፤ ማምረቻ እና የጦር ትጥቅ ጥገና ጣቢያ ማድረጉን ነው ወቅታዊ መረጃ ማጣሪያው የገለጸው።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ