የካቲት 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የመከላከያ ሕብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ ሠራዊቱ በፈፀማቸው ውጊያዎች የማይተካ ሚና ተጫውቷል ሲሉ የኢፌዴሪ ጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ ተናገሩ።
ኢትዮጵያን ለማዳን በተካሄደው የኅልውና ዘመቻ እና በሥራ አፈፃፀማቸው የላቀ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የሎጀስቲክስ የሠራዊት አባላት የማዕረግ እድገት፣ የሜዳይ፣ የእውቅናና የምሥጋና ሥነ-ሥርዓት ተከናውኗል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እንዳሉት የመከላከያ ሕብረት ሎጀስቲክስ ዋና መምሪያ የተቋሙን 80 በመቶ ሃብት የያዘና በውስጡ በርካታ የሙያተኛ ስብጥር በመያዙ ውግያን በመደገፍ ያስመዘገበው ስኬት የላቀ ነው፡፡
ከሕግ ማስከበር ዘመቻው በፊት ሽብርተኛው ሕወሓት በዋና መምሪያው ስር የሰገሰጋቸው አባላቶች የሎጀስቲክስ ድጋፍ ሥራውን ለማደናቀፍ የሸረቡትን ሴራ በአጭር ጊዜ በማምከን ዋና መምሪያውን በአዲስ አደረጃጀት አዋቅሮ ለተልዕኮ ማዘጋጀት የሎጀስቲክስ አመራሩ ውጤት በመኾኑ ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል፡፡
የመከላከያ ሕብረት ሎጅስቲክስ ዋና መምሪያ ኃላፊ ሌተናል ጀነራል አብዱራህማን ኢስማኤል በበኩላቸው ሀገርን ለማዳን በተደረገው ውጊያ አሸባሪው ቡድን ከጥቅም ውጪ ያደረጋቸውን ከቀላል እስከ ከባድ ተሸከርካሪዎችና መሳሪያዎችን በመማረክና ከደበቀበት ጫካ በመልቀም ጠግኖ ወደ ሥራ በመመለስ ሠራዊቱ እንዲጠቀምባቸው ማድረግ መቻሉን ገልፀዋል፡፡
የሎጀስቲክስ አባላት ቀን ከሌት ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለሠራዊቱ የሚያስፈልጉ በርካታ ሎጀስቲካዊ አቅርቦቶችን በወቅቱ በማድረስ ሠራዊቱ ለሚያደርጋቸው ውጊያዎች የጀርባ አጥንት በመኾን ማገልገላቸውንም ሌተናል ጀነራል አብዱራህማን እስማኤል ተናግረዋል፡፡
በሥራ አፈጻፀማቸው አጥጋቢ ውጤት አስመዝግበው የማዕረግና የሜዳይ ሽልማት የተበረከተላቸው አባላት በሰጡት አስተያየት ሽልማቱና የእውቅና አሰጣጡ በቀጣይ ለሚጠበቅባቸው ተልእኮ ግዳጃቸውን በከፍተኛ ኃላፊነትና ተነሳሽነት ለመወጣት እንደሚያነሳሳቸው ገልፀዋል፡፡
በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የማዕረግ ዕድገት፣ የሜዳይና የእውቅና ሰርተፍኬት ለሎጀስቲክስ ሙያተኞች ተሰጥቷል። በኅልውና ዘመቻው ላይ የበኩላቸውን ድጋፍ ላበረከቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቶች፣ ለተለያዩ ሲቪል ተቋማትና ድርጅቶች የእውቅናና የምሥጋና የምስክር ወረቀት መሰጠቱን ከመከላከያ ሠራዊት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/