❝የሉዓላዊነታችን የመጨረሻው ምሽግ የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በሰው ኃይልና በሎጀስቲክ ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው ኃላፊነት ነው❞ የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሞላ መልካሙ

0
117

ጎንደር: መስከረም 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ❝ከአንድ ቤተሰብ አንድ ዘማች❞ በሚል መሪ መልዕክት በጎንደር ከተማ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።

በሕዝባዊ መድረኩ የሃይማኖት አባቶች፤ የሀገር ሽማግሌዎችና ልዩ ልዩ የማኅበረሰብ ተወካዮች ተሳትፈዋል።

የከተማ አሰተዳደሩ ከንቲባ ሞላ መልካሙ ❝የሉዓላዊነታችን የመጨረሻው ምሽግ የሆነውን የሀገር መከላከያ ሠራዊት በሰው ኃይልና በሎጀስቲክ ማጠናከር ወቅቱ የሚጠይቀው ኃላፊነት ነው❞ ብለዋል።

የመከላከያ ሠራዊት ሀገር የገጠማትን የህልውና አደጋ በመቀልበስ ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ወጣቶች የሀገር መከላከያ ሠራዊትን እንዲቀላቀሉ ኅብረተሰቡ የማስተባበር ሥራን ማከናወን ይጠበቅበታል ነው ያሉት።

ለሀገር መከላከያ ሠራዊት የሚቀላቀሉ ወጣቶችን በመመልመሉ ሥራ የጎንደርና አካባቢው ወጣት መከላከያን በመቀላቀል ሀገርን ለማስቀጠል እየተገነባ ያለው ሠራዊት አባል በመሆን የታሪኩ አካል ልትሆኑ ይገባል ሲሉ ከንቲባ ሞላ መልካሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ዘጋቢ:- ጳውሎስ አየለ- ከጎንደር

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m