❝አንድ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ሀገራዊ ችግሮቻችንን በምክክርና በመነጋገር መፍታት ያስፈልጋል❞ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

148

ባሕር ዳር: ግንቦት 29/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን ከአማራ ክልል ከፍተኛ የሥራ ኀፊዎች ጋር የትውውቅ መርኃግብር እያካሄደ ነው።
በመድረኩ ላይ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያና ሌሎች አባላትም ተገኝተዋል።
ከአማራ ክልል የተውጣጡ የሀገር ሽማግሌዎች፣ እናቶች እና ወጣቶችም ተሳታፊ ናቸው።
የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ❝አንድ ጠንካራ ሀገር ለመገንባት ሀገራዊ ችግሮቻችንን በምክክርና በመነጋገር መፍታት ያስፈልጋል❞ ብለዋል።
ልዩነታችንን በማጥበብና በመቻቻል የተመሠረተች ጠንካራ ሀገር እንድትኖረን የአማራ ክልል መንግሥት ከሀገራዊ ምክክሩ ጎን በመኾን አስፈላጊውን ድጋፍ ያደርጋል ሲሉም ርእሰ መሥተዳድሩ ገልጸዋል።
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ሰብሳቢ ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ ኮሚሽኑ ኢትዮጵያ ውስጥ የሚለያዩንን አጀንዳዎች ለመቀነስ እና አንድነትን ለማጠናከር አልሞ የተቋቋመ ነው ብለዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/