❝አሚኮ ኅብር ኹለተኛው የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቴሌቪዥን ቻናል ሥርጭት የፊታችን ሰኞ ይጀምራል❞ የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አንተነህ መንግሥቴ

0
77

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 10/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን (አሚኮ) ኹለተኛ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሰኔ 13/2014 ዓ.ም ሥርጭቱን እንደሚጀምር የኮርፖሬሽኑ ምክትል ሥራ አስፈጻሚ አንተነህ መንግሥቴ ገልጸዋል።
አቶ አንተነህ በመግለጫቸው አሚኮ አሁን ላይ በሰባት ቋንቋዎች የሥርጭት ሽፋን እንዳለው ተናግረዋል። በዚህም በሀገር ውስጥ ቋንቋዎች አማርኛ፣ አዊኛ፣ ኽምጣና፣ ኦሮምኛ እና ትግርኛ ሲኾኑ ከውጭ ቋንቋዎች ደግሞ እንግሊዝኛ እና አረብኛ ሥርጭት እያስተላለፈ ይገኛል።
አሚኮ በአማራ ክልል በሚገኙ የብሔረሰብ ቋንቋዎች ማለትም ኽምጣና፣ አዊኛ እና ኦሮምኛ በሬዲዮ ዘርፍ የመረጃ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ከ17 ዓመት በፊት በ1997 ዓ.ም ሲኾን በጋዜጣ ደግሞ ከ2003 ዓ.ም ጀምሮ እንደኾነ ምክትል ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። በነዚህ ቋንቋዎች በ2009 ዓ.ም የቴሌቪዥን ሥርጭት ተጀምሮ የክልሉን ሕዝብ ባሕል፣ እሴት እና ቋንቋ ይበልጥ ለማሳደግ እየተሠራ እንደሚገኝም ተናግረዋል።
ከሰኔ 13/2014 ዓ.ም ጀምሮ ደግሞ ተደራሽነቱን በማስፋት ብዝኃነትን ለማዳበር የሥርጭት ቋንቋዎችን ጨምሮ “አሚኮ ኅብር” በሚል ስያሜ የቴሌቪዥን ጣቢያ ሥርጭት ማስተላለፍ ይጀምራል ብለዋል።
የፊታችን ሰኞ አሚኮ ኀብር ኹለተኛውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የቴሌቪዥን ቻናል ሥርጭት ሲጀምር ሦስት የኢትዮጵያ ቋንቋዎችን በመጨመር የሥርጭት አድማሱን ወደ አስር ቋንቋዎች ያሳድጋል ብለዋል።
በአዲስ የሚጀመሩትም ሶማሊኛ፣ ጉምዝኛ እና አፋርኛ ቋንቋዎች እንደኾኑ ተናግረዋል።
“ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን” በሚል መሪ ሐሳብ የሚታወቀው አማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን የሥርጭት አድማሱን እና የመረጃ አገልግሎት መስጫ ቋንቋዎችን የበለጠ ማስፋቱን ገልጸው ለአሚኮ አድማጭ፣ ተመልካችና አንባቢዎች በሙሉ የእንኳን ደስ ያላችሁ መልዕክትም አስተላልፈዋል።
በቀጣይም ጥናት ተሠርቶ ሌሎችን የኢትዮጵያ እና የውጭ ቋንቋዎችን ለማካተት እየተሠራ እንደኾነ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚው አመላክተዋል።
ዘጋቢ:- አሚናዳብ አራጋው
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/