❝በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደመውን ሃብት መልሶ ለመገንባት የክልሉ መንግሥት እየሠራ ነው፤ መልሶ በማቋቋም ሂደትም የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት እገዛ ለማድርግ ቁርጠኛ ናቸው❞ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር)

0
48

ታኅሣሥ 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) የተመራው ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በደሴ እና ኮምቦልቻ ከተሞች በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን የደረሰውን የመንግሥት እና የግል ተቋማት ውድመት እና ዘረፋ ተመልክቷል።

የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች በትምህርት፣ በጤና፣ በፋብሪካዎች፣በሆቴሎች እና ሌሎች ተቋማት የደረሰውን ውድመት እና ዘረፋ ነው የተመለከቱት።

የደረሰውን ውድመት እና ዘረፋ ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል። ርእሰ መሥተዳደሩ በመግለጫቸው አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ ክልል በወረራቸው አካባቢዎች ሁሉ በመግደል፣በማፈናቀል፣ በመዝረፍ እና በማውደም እኩይ ድርጊቱን አሳይቷል ብለዋል። ተግባሩም እውነተኛ ዘራፊ፣አውዳሚ እና ወንጀለኛ ቡድን መሆኑን ያስመሰከረበት ነው ብለዋል።

ወራሪውና አሸባሪው ቡድን ከመነሻው ጀምሮ አማራን በማዳከም ኢትዮጵያን ለማፍረስ ቆርጦ የመጣ ነው፤ በአረመኔያዊ ሥራም ትክክለኛ ማንነቱን የገለጠበት መሆኑን አስመስክሯል፤ እኛም ማረጋገጥ የቻልነው ይህንን ነው፤ ሕዝቡም የደረሰውን ውድመት እና ዘረፋ በመረዳት ያለ ምህረት ሊታገለው እንደሚገባ ገልጸዋል።

የሽብር ቡድኑ በሥራ ኃላፊዎች ባልተጎበኙ መሠል ተቋማት ላይም ሰፊ ጥቃት አድርሷል ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ የወደመውን ሀብት እና ንብረት በክልሉ እና በኢትዮጵያ ሕዝቦች እንዲሁም በመንግሥት እና በሌሎች አካላት ርብርብ መልሶ መገንባት የሚቻል ነው ብለዋል።

የመንግሥት ተቋማት አገልግሎት እንዲሰጡ በየደረጃው ያለው አመራር ወደ ሥራ እየገባ ነው፤የመንግሥት ሠራተኞችም ሥራ እንዲጀምሩ ይደረጋል ነው ያሉት፡፡

የክልሉ መንግሥትም ክልላዊ መልሶ ማቋቋም እና ግንባታ እቅድ አዘጋጅቶ እየሠራ ነው፤ መልሶ በማቋቋም ሂደትም የፌዴራል እና የክልል መንግሥታት እገዛ ለማድርግ ቁርጠኛ ናቸው ብለዋል።

የተዘረፉ ሀብቶች ቆጠራ እንደሚካሄድም በመግለጫቸው አንስተዋል፡፡

ርእሰ መሥተዳድሩ በመግለጫቸው ወጣቶችም የደረሰውን ዝርፊያ፣ውድመት እና ኢ-ሰብዓዊ ድርጊት በመገንዘብ ጠላትን ሊፋለሙ እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡ ወጣቶች መከላከያ ሠራዊት እና ልዩ ኃይል በመቀላቀል የሀገር ኅልውናን ማስጠበቅ እንደሚገባቸውም አስገንዝበዋል።

በቀጣይም የአማራ እና የኢትዮጵያ ነፃነት ማወጅ የሚቻለው ወራሪ ቡድኑን #በማጥፋት ነው፤ባለፈው ነገር መተከዝ አያስፈልግም፤ለወደፊቱ መሰል ጥቃት እንዳይደርስ መደራጀት ያስፈልጋል ብለዋል።

በርካታ አካባቢዎችም ነፃ እየወጡ ናቸው ያሉት ርእስ መሥተዳድሩ ጠላትን ሙሉ በሙሉ እስከ ወዲያኛው #ለማጥፋት ከፍተኛ ትግል ማድረግ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ሕዝቡ ከሚያደርገው የኅልውና ትግል ጎን ለጎን አካባቢውን ተደራጅቶ መጠበቅ እና ልማት ማስቀጠል እንደሚገባውም ተናግረዋል።

በወረራ ወቅት ወገንን በመክዳት ከወራሪ በድን ጋር የተሰለፉትን ከሃዲዎች በመያዝ ለሕግ ማቅረብ እንደሚገባም አሳስበዋል።

መንግሥትም ወንጀሎኞችን አጣርቶ እርምጃ እንደሚወስድ አረጋግጠዋል።

ዘጋቢ፦ አዳሙ ሽባባው -ከደሴ

#ተነሳ!!
#መሪህን ተከተል!!
#ሀገርህን አድን!!
#ነፃነትህን አትስጥ !!
#አካባቢህን ጠብቅ!!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation