❝ሀገራችን የገጠማትን የኅልውና አደጋ በተሟላ ድል የምታጠናቅቀው በጦርነቱ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማጎልበት የሚስተዋሉ መዛነፎችን በማረም ነው❞ አቶ አብርሃም አለኸኝ

0
100

ታኅሣሥ 25/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በአማራ ክልል የምሥራቅ ጎጃም፣ የምዕራብ ጎጃም፣ የአዊ ዞን እና የባሕር ዳር ከተማ መካከለኛ አመራሮች 2ኛ ዙር የምክክር መድረክ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው፡፡
የምክክር መድረኩ ዓላማ በየደረጃው ያለ አመራር በጦርነቱ የነበሩ ጥንካሬዎችን እና አንዳንድ መዛነፎችን በማረም ለቀጣይ ተልዕኮ ማዘጋጀት እና ማብቃት ነው ተብሏል፡፡
በዕለቱ በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ዘርፍ አስተባባሪ አቶ አብርሃም አለኸኝ ❝ሀገራችን የገጠማትን የሕልውና አደጋ በተሟላ ድል የምታጠናቅቀው በጦርነቱ የነበሩ ጥንካሬዎችን በማጎልበት የሚስተዋሉ መዛነፎችን በማረም ነው❞ ብለዋል።
ሀገራችን የገጠማት ጦርነት መላዉ ኢትዮጵያውያን፣ ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች በሰው ኃይል፣ በግብዓትና በሞራል በመሳተፋቸው ጦርነቱን በድል ማጠናቀቅ ችለናል፤ ነገር ግን ከድል በኋላ የሚስተዋሉ አንዳንድ መዛነፎች ስላሉ በፍጥነት መስተካከል አለባቸው ነው ያሉት።
አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና አፋር ክልል ወረራ ሲፈጽም የሀገሪቱን መውጫ እና መግቢያ በሮች በመቆጣጠር ኅልውናዋን መገዳደርና ከውጭ ጠላቶች ጋር በመገናኘት ጦርነቱን ቀጣናዊ ለማድረግ፣ በሱዳን በኩል መውጫ ኮሪደር ማስከፈት፣ የአማራን ሕዝብ አንገት ማስደፋት እና ኢትዮጵያን ማፍረስ ነበር ግን አልተሳካላቸውም ብለዋል አቶ አብርሃም አለኸኝ በመልዕክታቸው።
ከድል በኋላ ባሉ የድኅረ ድል መዛነፎችን ማረም እና በመላው ሀገሪቱ የጋራ መግባባት መፍጠር እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
❝እንደሕዝብ የመጣውን ወራሪ ኃይል የመከትነው እንደሕዝብ መሆኑን መሰመር አለበት፤የትኛውም አካባቢ በተሰጠው አደረጃጀት የተሳፈ መሆኑን በመተማመን ለቀጣይ ተልዕኳችን ዝግጁ መሆን አለብን❞ ብለዋል።
የምክክር መድረኩ በሀገራዊና ክልላዊ ጉዳዮች ጥልቅ ውይይት ተደርጎ ለቀጣይ ተልዕኮ የሚያዘጋጅ መግባባት ላይ ይደረሳል ተብሎ እንደሚጠበቅ ከአማራ ብልጽግና ፓርቲ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣ እንገንባ፣ እንዘጋጅ‼
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/