ባሕር ዳር፡ የካቲት 22/2011 ዓ.ም(አብመድ) የኬንያው ፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነው ዛሬ የካቲት 22/ 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ የገቡት፡፡
ፕሬዚዳንቱ ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ጣቢያ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድን ጨምሮ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
ሁለቱ መሪዎች በሁለትዮሽ የኢኮኖሚ ጉዳዮች እንደሚመክሩ ይጠበቃል።
ኡሁሩ ኬንያታ በኢትዮጵያ ቆይታቸው በአዲስ አበባ በሚካሄደው የኢትዮ-ኬንያ ንግድና ኢንቨስትመንት ፎረም ላይ እንደሚሳተፉም ይጠበቃል።
በፎረሙ የሚሳተፉ 100 የኬንያ መንግስት ባለስልጣናት፣ የኮርፖሬት እና የንግድ ማህበረሰብ ተወካይ ኬንያዉያንም ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል።
የንግድ እና ኢንቨስትመንት ፎረሙ ዓላማ ደግሞ በኢትዮጵያ እና በኬንያ መካከል ያለውን የንግድ እና የኢኮኖሚ ትስስር ማጠናከር መሆኑን ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ፎቶ፡- ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት