ባሕርዳር: የካቲት 28/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ዘውዴ ለአዲሱ የናይጄሪያ ፕሬዚዳንት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡
በቅርቡ በናይጄሪያ በተካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ቦላ ቲኑቡ ማሸነፋቸው ይታወሳል፡፡

ፕሬዚዳንት ሣኅለ ወርቅ ምርጫው በኢትዮጵያ እና በናይጄሪያ መካከል ያለውን ለረጅም ጊዜ የቆየና ጠንካራ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ያገለግላል የሚል እምነት እንዳላቸው ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!