ፋሲል ከነማ እና ዳሽን ቢራ አብሮ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ውል ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት አራዘሙ፡፡

0
217

አዲስ አበባ፡ የካቲት 21/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ዳሽን ቢራ ከፋሲል ከነማ ጋር ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት በጋራ ለመሥራት የሚያስችለውን የ136 ሚሊየን ብር የስምምነት ውል ተፈራርመዋል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የገቢ ማስገኛ መርኃግብሮችን በጋራ እንደሚያዘጋጁ ተገልጿል። የክለቡ ውጤት እየታየም ተጨማሪ ማበረታቻዎች ይኖራሉ ተብሏል።
ባለፈው ዓመት ፋሲል ከነማ የፕሪሚየር ሊጉ አሸናፊ መኾኑ ይታወሳል። በዚህ ውስጥ ደግሞ የዳሽን ቢራ አጋርነት ሚናው ከፍተኛ ነበር ነው የተባለው።
የዳሽን ቢራ ማርኬቲንግ ዳይሬክተር አቶ አብርሃም ዘሪሁን ዳሽን ቢራ ላለፉት ዓመታት ማኅበራዊ ኃላፊነቱን ሲወጣ ቆይቷል ብለዋል። 800 ሚሊየን ብር በላይ ለማኅበረሰብ አገልግሎት ፈሰስ አድርጓል ነው ያሉት። በቀጣይም ፋሲል ከነማ ያለውን ጥንካሬ ይዞ እንዲቀጥልና ለበለጠ ስኬት እንዲበቃ አብረው እንደሚሠሩ ገልጸዋል፡፡
የፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ሥራ አስኪያጅ አቶ አቢዮት ብርሃኑ በፋሲል ስኬት ውስጥ የዳሽን ቢራ አስተዋጽኦ ከፍተኛ ነበር ብለዋል። በተደረገው ስምምነት ደስተኛ መኾናቸውንም ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
ዳሽን ቢራ ላለፉት አምስት ዓመትም የፋሲል ከነማ አጋር ኾኖ መቆየቱ ይታወቃል።
ዘጋቢ፡- ባዘዘው መኮንን -ከአዲስ አበባ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/