ጥምቀትን በጎንደር በልዩ ድምቀት ለማክበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ አስታወቀ፡፡

0
32

ባሕርዳር፡ ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ጥር 11/2014 ዓ.ም በድምቀት የሚከበረው የጥምቀት በዓል በጎንደር ልዩ ድምቀት አለው፡፡ ከምእመናኑ ባለፈ ከሀገር ውስጥም ሆነ ከውጭ ሀገራት በመጡ ታዳሚዎች ታጅቦ በየዓመቱ የሚከበረው ጥምቀት በጎንደር ዘንድሮም ድምቀቱን እንደጠበቀ እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት መደረጉን የአማራ ክልል ቱሪዝም ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮው ኀላፊ አቶ ጣሂር ሙሃመድ በሰጡት መግለጫ የሀገራቸውን ጥሪ ተቀብለው የመጡ ዲያስፖራዎች ለዘንድሮው በዓል ልዩ ድምቀት እንደሚሆኑም ጠቅሰዋል። ይህንን ከግምት ያስገቡ መርሃ ግብሮች እንደተዘጋጁም አስታውቀዋል።

በነገው እለት በባሕርዳር ከተማ ታላቅ ሲንፖዚየም እንደሚካሄድ እና በአሽባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል ነው ያሉት።

የኢንቨስትመንት አማራጮችም እንደሚገለጹ የተናገሩት አቶ ጣሂር በእለቱም የአንድነት እና የትብብር ማዕድ ማጋራት ሥነ ስርዓት መዘጋጀቱን አስታውቀዋል።

ኀላፊው በቀጣይም ጥምቀትን በጎንደር ለማክበር ለሚመጡ እንግዶች የተለያዩ መርሃ ግብሮች ተዘጋጅተዋል ብለዋል። ከበዓሉ ቀደም ባሉ ቀናት በጎንደር የጎዳና ሩጫ፣ የንጉሥ እራት እና የዳግማዊ አፄ ቴዎድሮስ ሹሩባ አውደ ርዕይ እንደሚካሄድም አስረድተዋል።

ዘጋቢ:- የማነብርሃን ጌታቸው

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/