ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ የአፍሪካ ህብረት ሽልማትን ወሰዱ፡፡

139

 

ባሕር ዳር፡ የካቲት 05/2011 ዓ.ም(አብመድ) ዶክተር ዐብይ አህመድ የአፍሪካ ህብረት ሽልማትን ወስደዋል፡፡

Image may contain: 1 person

ሽልማቱ በስርዓተ ጾታ እኩልነት ዙሪያ ጥሩ ተግባራትን ለፈጸሙ ግለሰቦች የሚሰጥ መሆኑ ተገልጿል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ባሳለፍናቸው ወራት ውስጥ በአመራር ስፍራዎች ላይ የሴቶችን ተሳትፎ አሳድገዋል፡፡ ለአብነት የሚኒስትሮች ምክር ቤት ግማሽ አባላት ሴቶች እንዲሆኑ አድርገዋል፡፡ ሴት ፕሬዝደንት፣ መከላከያ ሚንስትር፣ የምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ እና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት መሾማቸው ተነስቷል፡፡

ሴቶች በሙስና ወንጀሎች የመሳተፍ እድላቸው አነስተኛ መሆኑን እና በስራቸው ውጤታማ መሆናቸውን በተደጋጋሚ እንደተናገሩ ተገልጿል፡፡ በስርዓተ ጾታ አቀንቃኞች ዘንድ ዶክተር ዐብይ እንደሚወደሱም ተመላክቷል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ያገኙት ሽልማት በአፍሪካ ህብረት እና በመንግስታቱ ድርጅት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በጋራ የሚዘጋጅ መሆኑ ተነግሯል፡፡

ምንጭ፡ አፍሪካ ኒውስ

በቢኒያም መስፍን