ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በአርሲ ዞን ሄጦሳ ወረዳ በመስኖ የለማ የስንዴ ማሳን እየጎበኙ ነው።

0
507
ባሕር ዳር፡ ጥቅምት 03/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በጉብኝቱ የቀድሞ ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኀይለማርያም ደሳለኝን ጨምሮ ከፍተኛ የፌዴራልና የክልል የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶክተር) በጉብኝቱ ላይ ከዚህ በፊት የማይታረሱ መሬቶችን በማረስ በኩታ ገጠም እርሻ በስንዴ ምርት እራሳችንን ለመቻል ሰፊ ሥራዎችን እየሠራን ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ የግብርና ልማታችን የእድገታችን መሰረት ስለሆነ ልዩ ትኩረት በመስጠት ይሠራል ያሉ ሲሆን በግብዓትና በገበያ ትስስር ውጤታማ እንዲሆን ይደረጋል ብለዋል።
የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ ዘንድሮ በክልሉ ከሚመረተው የስንዴ ምርት ውስጥ 74 በመቶ በኩታ ገጠም የሚመረት ነው ማለታቸውን ፋብኮ ዘግቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ