ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ደቡብ ሱዳን ገቡ።

143
ባሕርዳር: መጋቢት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት በዛሬው ዕለት ደቡብ ሱዳን ጁባ ከተማ ገብተዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጁባ ሲደርሱ የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር ማያርዲት አቀባበል እንዳደረጉላቸው ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ሁለቱ መሪዎች በሀገራቱ መካከል ስላለው የሁለትዮሽ ግንኙነት እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!