ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር የስልክ ውይይት አደረጉ።

0
419

ባሕር ዳር፡ ጥር 02/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ግልፅ የስልክ ውይይት ማድረጋቸውን አስታውቀዋል።

ከፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር በተለይም በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ መነጋገራቸውን ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሰሜናዊው የሀገራችን ከፍል የሕግ የበላይነትን የማስከበር ክንውን የሚገኝበትን ደረጃ እንዲሁም የሰብዓዊ ዕርዳታ፣ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮችና በቅርቡ ነፃ በወጡ አካባቢዎች የሚደረገውን መልሶ የመገንባት ርብርብ አስመልክቶ መንግሥት አያደረገ ያለውን ጥረት ለፕሬዚዳንቱ ገልጸዋል።

መሪዎቹ የሀገራቱን የሁለትዮሽ ግንኙነት ለማጠናከር እና በጋራ ጉዳዮች ላይ በትብብር ለመስራት መነጋገራቸውም ተመላክቷል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/