ግድያው አሁንም እንዳልቆመ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡

202
ነጭመደበኛ
ነጭመደበኛ
ግድያው አሁንም እንዳልቆመ በመተከል ዞን ድባጤ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ተናገሩ፡፡
ባሕር ዳር፡ ኅዳር 11/2013 ዓ.ም (አብመድ)
በመተከል ዞን ከግድያ የተረፉ ዜጎችን የፌዴራል ፖሊስ በጸጥታ ጉዳይ ላይ እንዳወያያቸው ተፈናቃዮች ገልጸዋል፡፡ በወይይቱም በግድያው ምክንያት ትተውት የመጡት ሃብት እና ንብረት የተዘረፈ በመሆኑ ችግር ላይ መውደቃቸውንና አሁንም የሰው ህይወት እየጠፋ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ከነበሩበት ቀበሌ መፈናቀላቸውንና ቤት ንብረታቸው መውደሙን በውይይቱ እንዳነሱ ለአብመድ በስልክ ገልጸዋል።
አሁን ላይ ችግር ላይ መውደቃቸውን የተናገሩት ተፈናቃዮቹ የጸጥታው ጉዳይ መፍትሄ የሚያገኝ ከሆነ በጊዜያዊ መጠለያ ቢሆን ወደ ቀያቸው ተመልሰው የመኖር ፍላጎት እንዳላቸው ነው የገለጹት፡፡
የጥቃቱን አለመቆምና ለተፈናቃዮች እየተደረገላቸው ያለውን ድጋፍ ለመጠየቅ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሰላም ግንባታና ደህንነት ቢሮ እንዲሁም የምግብ ዋስትና እና አደጋ መከላከል ጽህፈት ቤት የስራ ኃላፊዎች በተደጋጋሚ ስልክ ብንደውልም ሊያነሱ አልቻሉም፡፡ መረጃውን እንዳገኘን የምናደርስ ይሆናል።
ዘጋቢ፡- አዳሙ ሽባባው
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here