“ጊዜው የህዳሴው ግድብ ለሶስቱ ሀገራት የሰላም፣ የትብብር እና የአብሮ መኖር ተምሳሌትነቱን የምናሳይበት ነው” ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ

0
53

ባሕር ዳር፡ ጥር 12/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጊዜው ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ለኢትዮጵያ፣ ግብፅ እና ሱዳን የሰላም፣ የትብብር እና የአብሮ መኖር ተምሳሌትነቱን የምናሳይበት ነው ሲሉ ገልፀዋል።

ኢትዮጵያ በግብርና፣ በማምረቻው ዘርፍ እና በኢንዱስትሪ ላይ የተመሰረተ ዘመናዊ ኢኮኖሚ ለመገንባት ያላትን ህልም ለማሳካት የምትችለው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅሟን ማሳደግ ስትችል ብቻ እንደሆነ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ጠቁመዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኀበራዊ ዘርፍ በኩልም ጥራት ያለው ትምህርት፣ የጤና አገልግሎት እና ንፁህ የመጠጥ ውኃ ለዜጎች ለማቅረብ በቁርጠኝነት እንደሚሰራም አንስተዋል።

ኢትዮጵያ በመልከዓ ምድራዊ አቀማመጧም ሆነ ባላት የውኃ ሀብት ያላትን ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍላጎት ለማሟላት የውኃ ኃይሏን መጠቀም እንደሚገባትም ጠቅላይ ሚኒስትሩ የህዳሴ ግድቡን አስመልክቶ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባወጡት መግለጫ ጠቁመዋል።

በአሁኑ ወቅት 53 በመቶ ወይንም ወደ 60 ሚሊዮን የሚሆኑ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተጠቃሚ አለመሆናቸውን የጠቆሙት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ያለ ኤሌክትሪክ የትኛውም አገር ዘላቂ ልማት እና እድገት ሊያረጋግጥ አልቻለም ብለዋል።

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/