“ድህረ ምርጫ ሰላማዊ ኾኖ እንዲቀጥል እየሠራን ነው” የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ

0
69
“ድህረ ምርጫ ሰላማዊ ኾኖ እንዲቀጥል እየሠራን ነው” የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ
ባሕር ዳር፡ ሰኔ 15/ 2013 ዓ.ም (አሚኮ) የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ተወካይ ኀላፊ ኮማንደር ብዙነህ አጎናፍር 1 ሺህ 128 ምርጫ ጣቢያዎች በዞናችን አሉን፤ ቁሳቁስም በአግባቡ ከደረሱ በኋላ ጥብቅ ጥበቃ ተደርጎ ያለምንም ችግር ምርጫ ተካሂዷል ብለዋል።
በምርጫ ሂደቱ ባሉ እንቅስቃሴዎች የጸጥታ አባላት በተሰማሩበት ውጤታማ ተግባር ፈጽመዋል።
ምንም እንኳን በዚህ መልክ ሰላማዊ ተግባር ብንከውንም ከምርጫ ሕግ ውጭ የሆኑ ተግባራት ግን ደግሞ የምርጫ ሂደቱን ያወኩ ችግሮችም ተስተውለው ነበር ብለዋል ኮማንደሩ።
በምንጃር ሸንኮራ ወረዳ በምርጫው ዕለት ሲቀሰቅስ ተገኝቶ የነበረ ግለሰብ የ8 ሺህ ብር ቅጣት ተወስኖበታል ነው ያሉት።
ሌላው በመንዝ ቀያም ሲቀሰቅስ በተገኘ ግለሰብ ላይ ምርመራ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡
በተለይም ከግንዛቤ ማነስ አኳያ የተወዳዳሪ ፓርቲዎችን መለያ ለብሶ የመገኘት ችግሮች ነበሩ ያሉት ኮማንደሩ ችግሮችን በማረም እንደ ዞን ሰላማዊ ምርጫ ተካሂዷል ነው ያሉት።
በሕዝቡና በጸጥታ ኀይሉ የተቀናጀ ተግባር ውጤታማ ሥራ መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ በቀጣይ በድህረ ምርጫውም ሰላም የማስጠበቅ ተግባር ተጠናክሮ እንደሚቀጥል አብራርተዋል፡፡
ውጤት የሕዝብ ነው የሚያሸንፈውም ሕዝብ ነው፤ ችግሮች ቢከሰቱም በበቂ ሁኔታ ዝግጅት አድርገናል ብለዋል፡፡
ዘጋቢ፡- እንዳልካቸው አባቡ – ከደብረ ብርሃን
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here