ባሕር ዳር፡ ጥር 07/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የዳያስፖራ ሲምፖዚየም ባሕርዳር እየተካሄደ ነው፡፡ በሲምፖዚየሙ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ርእሰ መሥተዳድር ይልቃል ከፋለ (ዶ.ር) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በአማራ እና በአፋር ክልል ሰብዓዊ እና ቁሳዊ ጉዳት አድርሷል፤ ይህን ቡድን ለመመከት እና ድልን ለመቀዳጀት መስዋእትነት ተከፍሏል ብለዋል።
የሽብር ቡድኑ ባደረሰው ወረራ በርካቶች ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው የሰው እጅ እያዩ ባሉበት በዚህ ወቅት የኢትዮጵያ ሕዝብ በአንድነት የሽብር ቡድኑን በግንባር ከመደምሰስ ባሻገር ለተፈናቀሉ ወገኖች አለኝታነታቸውን አሳይተዋል ነው ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ፡፡
ዳያስፖራው የሀገሩን እውነት ለዓለም በማሳየት ያደረገው አስተዋጽኦ ከፍተኛ መሆኑን የጠቀሱት ርእሰ መሥተዳድሩ ለዚህም ክብርና ምስገና እንደሚገባ ገልጸዋል፡፡
ዳያስፖራው ወገኑን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ ተቋማትን ለመገንባት በሚደረገው ርብርብ የድርሻውን እንዲወጣም ጥሪ አቅርበዋል።
ዶክተር ይልቃል ዳያስፖራው ከዲፕሎማሲው ጎን ለጎን በኢኮኖሚ ዘርፉ በመሳተፍ ራሱንም በመጥቀም ለሀገሩ አስተዋጽዖ እንዲያበረክት የተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች መዘጋጀታቸውን አብራርተዋል።
በሲምፖዚየሙ ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሔራዊ ደኅንነት አማካሪ ሚኒስትር አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን ጨምሮ፣ ምክትል ርእሰ መሥተዳድር ጌታቸው ጀምበር (ዶ.ር)፣ የክልል እና የፌዴራል ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች እና የዳያስፖራ አባላት ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ትርንጎ ይፍሩ
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/