ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 3 ሺህ 110 ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል፡፡

0
35

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በልዩ ልዩ የትምህርት መስኮች ያስተማራቸውን 3 ሺህ 110 ተማሪዎችን ነገ ያስመርቃል፡፡

ባሕር ዳር፡ ሰኔ 21/2013 ዓ.ም (አሚኮ) ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በ19 የትምህርት ኮሌጆች ሲያስተምራቸው የቆዩትን 3 ሺህ 110 ተማሪዎችን ነገ እንደሚያስመርቅ የዩኒቨርሲቲው የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አሕመድ ሙሐመድ ተናግረዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው ለ13ኛ ዙር በመጀመሪያ ዲግሪ 3 ሺህ 72፣ በሁለተኛ ዲግሪ 36 እንዲሁም በሦስተኛ ዲግሪ ደግሞ 2 ተማሪዎችን ነው የሚያስመርቀው፡፡

ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ነገ የሚመረቁትን ጨምሮ ከ26 ሺህ በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

ዘጋቢ፡- ኤሊያስ ፈጠነ-ከደብረብርሃን

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2HYJBLZ
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here