ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡

0
119
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ከመተከል ለተፈናቀሉ ወገኖች ድጋፍ አደረገ፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 03/2013 ዓ.ም (አብመድ) የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመጀመሪያ ዙር ድጋፉ በድርቆሽ መልክ የተዘጋጀ እንጀራ ለደራሽ ምግብነት በፍጥነት እንዲውል ወደ ቦታው እያጓጓዘ ነው፡፡
በቀጣይነትም የችግሩ ሥር ነቀል የመፍትሄ አካል ለመሆን ያለውን ዝግጁነት ገልጿል።
ዩኒቨርሲቲ ከዚህ ቀደምም በአንበጣና በጎርፍ ለተጎዱ የወሎና የአፋር አካባቢዎች ድጋፍ የሚውል ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በህግ ማስከበር ዘመቻውም ለመከላከያ ሰራዊት፣ ለአማራ ልዩ ኀይልና ሚሊሻ ከ4 ሚሊዮን ብር በላይ የምግብና የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጎ እንደነበርም ከዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ ትስስር ገጽ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here