ባሕርዳር : ግንቦት 22/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያ በመጀመርያው ዙር ከቻድ ጋር ስትደለደል የሁለቱ ሀገራት አሸናፊ በሁለተኛ ዙር ማጣርያ ከናይጄርያ ጋር የሚጫወት ይኾናል።
አራት ዙሮች ባሉት ማጣርያ የአንደኛ ዙር ማጣርያ ጨዋታዎች ከሐምሌ 3 እሰከ 11/2015 ዓ.ም ባሉት ቀናት ይደረጋሉ።
2024 ኦሊምፒክ ጨዋታዎች የሴቶች እግር ኳስ የአፍሪካ ዞን የማጣርያ ጨዋታዎች እጣ ማውጣት ሥነ-ሥርዓት ግብጽ ካይሮ ላይ መካሄዱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!