የፖኪስታን ንግድና ኢንቨስትመንት ልዑክ አዲስ አበባ ገባ።
ባሕርዳር: የካቲት 26/2015 ዓ.ም (አሚኮ) የፖኪስታን ንግድና ኢንቨስትመንት ልዑክ በኢትዮጵያ የኢቨስትመንት አማራጮችን ለመጎብኘት ዛሬ ማምሻውን አዲስ አበባ ገብቷል።
ልዑኩ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች አቀባበል አድርገዋል።
ልዑኩ በተለያዩ ዘርፎች የተሰማሩ ከ70 በላይ ባለሃብቶችን ያካተተ መኾኑን ኢዜአ ዘግቧል። ለሚቀጥሉት አምስት ቀናትም በኢትዮጵያ ቆይታ የሚያደርግ መኾኑ ታውቋል ።

ግብርና ፣ አምራች ኢንዱስትሪ ፣ኢንፎርሜሽን ኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂ ፣ ማዕድንና ቱሪዝም ባለሃብቶቹ ከተሰማሩባቸው ዘርፎች መካከል ናቸው ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!