“የጥፋት ኀይሎች ኀብረተሰቡን እንደ መሳሪያ እንዳይጠቀሙበት በንቃት ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን መሥራት ይገባል።” የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች

0
112
“የጥፋት ኀይሎች ኀብረተሰቡን እንደ መሳሪያ እንዳይጠቀሙበት በንቃት ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን መሥራት ይገባል።” የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች
ባሕር ዳር: መጋቢት 19/2013 ዓ.ም (አብመድ) በኦሮሞ ብሔረሰብ አስተዳደር ከሚሴ ከተማ በወቅታዊ የሰላም ጉዳይ ዙሪያ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።
በሕዝባዊ ውይይቱ ላይ የብሔረሰብ አስተዳደሩና የከሚሴ ከተማ አስተዳደር የሥራ ኀላፊዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የከተማው ነዋሪዎች ተሳትፈዋል።
በሕዝባዊ መድረኩም የከሚሴ ከተማ ነዋሪዎች በተፈጠረው ችግር ማዘናቸውን በመግለፅ የጥፋት ኀይሎች ኀብረተሰቡን እንደ መሳሪያ እንዳይጠቀሙበት በንቃት ከፀጥታ መዋቅሩ ጋር በመሆን መሥራት እንደሚገባ ተናግረዋል።
ነዋሪዎቹ የአማራና የኦሮሞ ሕዝቦች በጋብቻና በባህል የተሳሰሩና ከጥንት ጀምሮ በአብሮነት የቆዩ መሆናቸውንም አንስተዋል።
የከሚሴ ከተማ ከንቲባ ኡመርዬ አስዋብ እንዳሉት በከተማ አስተዳደሩ አሁን ላይ አንፃራዊ ሰላም ተፈጥሯል። የከተመዋ ሰላም በዘላቂነት እንዲጠበቅም ሁሉም አካል ተባብሮ ሊሠራ እንደሚገባ አሳስበዋል።
የብሔረሰብ አስተዳደሩ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አህመድ ሀሰን በበኩላቸው ችግሩ ወደከፋ ደረጃ እንዳይሸጋገር የሀገር ሽማግሌዎችና የሃይማኖት አባቶች ላደረጉት አስተዋፅኦ አመስግነዋል።
አሁን ላይ በብሔረሰብ አስተዳደሩ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም አጠናክሮ ማስቀጠል እንደሚገባም ዋና አስተዳዳሪው አስገንዝበዋል።
ዘጋቢ:– ይማም ኢብራሂም
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here