“የጥምቀት በዓል የባርነት ደብዳቤ የተደመሰሰበት፣ ትህትና የተገለጠበት፤ ጸጋ የተወረሰበት ምስጢር ነው” ርእሰ መስተዳድር ዶክተር ይልቃል ከፋለ

0
53
ባሕር ዳር: ጥር 10/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ርእሰ መሥተዳደሩ ለጥምቀት በዓል ያስተላለፉት መልእክት።
እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሳችሁ!
ሀገራችን ኢትዮጵያ የበርካታ ባሕሎችና ሃይማኖታዊ እሴቶች እንዲሁም ታሪካዊ ቅርሶች ባለቤት ናት። በዓለም አደባባይ ጎልተንና ደምቀን ከምንታወቅባቸው ባሕላዊና ሃይማኖታዊ እሴቶቻችን መካከል የጥምቀት በዓል አንዱ ነው።
የጥምቀት በዓል የባርነት ደብዳቤ የተደመሰሰበት፣ ትህትና የተገለጠበት፤ ጸጋ የተወረስበት ምስጢር ነው።
በዓሉ የአንድነታችንና የአብሮነታችን መገለጫ ከመሆኑም በተጨማሪ የሀገርና የሕዝብ ሀብት እንዲሁም የዓለም ቅርስ ነው።
ቅርሱ ሃይማኖታዊ ሥርዓቱን ጠብቆ፤ ይበልጥ አድጎና ለምቶ የቱሪዝም መስህብ ሆኖ እንዲቀጥል ማድረግ አለብን።
ልዩ ልዩ በዓላትን በማልማትና በማስተዋወቅ ከቱሪዝም ዘርፉ የሚገኘውን ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ ለማሳደግ የጀመርነውን ሥራ አጠናክረን እንቀጥላለን።
በዓሉን ስናከብርም ከቂምና ጥላቻ ርቀን ትብብርና አብሮነት የምንገነባበት፣ ለእውነት የምንጸናበትና ለአካባቢያችን ሰላም በአንድነት የምንቆምበት ሊሆን ይገባል።
ስለሆነም ለእምነቱ ተከታዮች በሙሉ በዓሉ የመተሳሰብ፣ የመረዳዳት፣ የአብሮነትና የአንድነት እንዲሆንላችሁ በራሴና በክልሉ መንግሥት ስም እመኛለሁ።
መልካም በዓል!
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!