የጎንደር ከተማንና አካባቢዋን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ያለመ ውይይት ከባለሀብቶች እና ከአጋር አካላት ጋር እየተካሄደ ነው፡፡

0
52
የጎንደር ከተማንና አካባቢዋን የኢንቨስትመንት መዳረሻ ለማድረግ ያለመ ውይይት ከባለሀብቶች እና ከአጋር አካላት ጋር እየተካሄደ ነው፡፡
ባሕር ዳር፡ ጥር 13/2013 ዓ.ም (አብመድ) ውይይቱ የከተማዋን እና የአካባቢውን ዕምቅ የኢንቨስትመንት አማራጭ በማሳየት ዓልሚዎች የአካባቢውን የምጣኔ ሀብት እንቅስቃሴ ለመለወጥ በሚችሉበት ሁኔታ ላይ ትኩረት አድርጓል፡፡
በጎንደር ከተማ 168 የሚደርሱ አነስተኛ፣ መካከለኛና ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች በ4 የኢንዱስትሪ መንደሮች ውስጥ ይገኛሉ፡፡ በአሁኑ ወቅትም ከ400 ሄክታር በላይ መሬት የሚሸፍን 5ኛ የኢንዱስትሪ መንደር ለባለሀብቶች መዘጋጀቱን የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሞላ መልካሙ ገልፀዋል፡፡
በመድረኩ ላይ የተገኙት የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ፋንታ ማንደፍሮ ባለሀብቶች የአካባቢውን ፀጋ መሠረት አድርገው እንዲያለሙና የህዝቡን የኑሮ ሁኔታ እንዲለውጡ አሳስበዋል፡፡
ምክትል ርዕሰ መስተዳድሩ መንግሥት በኢንቨስትመንት ዘርፉ ላይ ያለውን የአገልግሎትአሰጣጥ ችግርንና የመሠረተ ልማት አቅርቦት ውስንነትን በማሻሻል ባለሀብቱን ለማገዝ ቁርጠኛ ነው ብለዋል፡፡
ባለሀብቶችም የወሰዱትንና የሚወስዱትን መሬት ቃል በገቡት መሠረት በፍጥነት እንዲያለሙ ጠይቀዋል፡፡ በውይይቱ ከፌዴራል የመጡ ሚኒስትር ዲኤታዎችና የመንግሥት የልማት ድርጅት ኃላፊዎች እንዲሁም ከሀገር ውስጥና ከውጭ የመጡ ባለሀብቶች እየተሳተፉ ነው፡፡
ባለሀብቶች ሊሰማሩባቸው የሚችሉ የኢንቨስትመንት አማራጮችም ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ነው፡፡
ዘጋቢ፡- አብርሃም አዳሙ – ከጎንደር
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በፌስቡክ https://bit.ly/2UwIpCw
በዌብሳይት www.amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here