ባሕር ዳር: ጥር 25/2015 ዓ.ም (አሚኮ) ኢትዮጵያውያን ሠንደቃቸውን አብዝተው ይወዷታል፣ ከነብሳቸው ያስበልጧታል፣ ደም እያፈሰሱ፣ አጥንት እየከሰከሱ ያፀኗታል፣ ነብሳቸውን ገብረው በኩራት ያውለበልቧታል።
በቃል ኪዳን የጸናች፣ ተስፋ የተጣለባት፣ አርበኞች እሷን አስቀድመው እየገሰገሱ ድል የሚነሱባት፣ ጠላቶቻቸውን የሚያንበረክኩባት ናት የኢትዮጵያ ሠንደቅ።
ሠንደቅ የሚከበርባት፣ ስለ ሠንደቅ መስዋዕትነት የሚከፈልባት ደብረ ታቦር ጎዳናዎቿን በአረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሠንደቅ አሸብርቃለች፣ ጎዳናዎቿን በሠንደቅ አሳምራ በዓለ መርቆሬዎስን እያከበረች ነው።
ዘጋቢ ፦ታርቆ ክንዴ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!