የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት በመሰብሰብ የምርት ብክነትን መከላከል እንደሚገባ ግብርና ቢሮ አሳሰበ፡፡

0
48
ባሕር ዳር፡ መስከረም 12/2013ዓ.ም (አብመድ) የደረሱ ሰብሎችን በፍጥነት በመሰብስብ በዝናብ እና በተለያዩ ነፍሳት ሊደርስ የሚችለውን ጉዳት መከላከል እንደሚገባ የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ አሳስቧል፡፡
የዝናቡ ስርጭቱ እስከ መስከረም መጨረሻ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የምዕራብ አማራ ሜትዮሮዎሎጅ አገልግሎት ማዕከል ማስጠንቀቁን ጠቀስን መዘገባችን ይታወሳል፡፡ ይህንም ተከትሎ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት ሊያደርስ ስለሚችል ቀድሞ በጥንቃቄ በመሰብሰብ እና በመውቃት በንጹሕ ማከማቻ ማስቀመጥ እንደሚገባ የግብርና ቢሮው አሳስቧል፡፡
በቢሮው የሰብል ልማት እና ጥበቃ ባለሙያ ኤሊያስ በላይ እንደገለጹት በዚህ ወቅት ምዕራብ እና ማዕከላዊ ጎንደር ዞኖች እና አዊ ብሔረሰብ አስተዳድር ሰፊ ሽፋን ያለው ሰሊጥ የሚደርስባው ናቸው፡፡ በእነዚህ አካባቢዎች ደግሞ እስከ መስከረም መጨረሻ የዝናም ስርጭት እንደሚኖር የሜትዮዎሮሎጅ ትንበያ ያሳያል፡፡ የዝናቡ መጠን በምርት ላይ ጉዳት አድርሶ የምርት ብክነት እና የጥራት ችግር እንዳይፈጠር በፍጥነት በመሰብሰብ ጥራት ባለው ማከማቻ ማስቀመጥ እንደሚገባ ባለሙያው አሳስበዋል፡፡
ዘጋቢ፡- ዳግማዊ ተሰራ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here