የዛሬ ውሎን የህልውና ዘመቻ አስመልክቶ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ የሰጡት አጭር መረጃ።

0
248
የዛሬ ውሎን የህልውና ዘመቻ አስመልክቶ የአማራ ክልል የመንግሥት ኮምዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት ዋና ዳይሬክተር ግዛቸው ሙሉነህ የሰጡት አጭር መረጃ።
አሸባሪውን የትህነግ ቡድን እስከወዲያኛው ለመደምሰስ ተጨማሪ የወዳጅ ኃይል በከፍተኛ የትግል ወኔ በሁሉም ግንባሮች በበቂ ስልጠና እና በዉጊያ ጥበብ የተካኑ ጀግና ታጋዮቻችን የትግል ሜዳው ላይ ተቀላቅለዋል።
በዛሬው እለትም አሸባሪው ትህነግ በሀገር መከላከያ ሠራዊታችን፣ በአማራ ልዩ ኃይልና ሚሊሻ ጠንካራ ክንድ እርምጃ እየተወሰደበት ይገኛል። በተለያዩ አውደውጊያ ግንባሮች በርካታ የጠላት ኀይል ተደምስሷል። ምን ያህሉ ተደመሰሱ የሚለውን ለመመለስ ከቁጥሩ መብዛት አንፃር ለመገመት ያስቸግራል።
የትግራይ እናቶች የትህነግን ባዶ ቀረርቶ ከሚሰሙ ልጆቻቸው የት እንዳሉ ቢጠይቁ ምላሹን ያውቁታል። ተገዶ የመጣው የትህነግ የህጻናት እና የእናቾች ቡድን አብዛኛው በሁሉም አውደውጊያ ግንባሮች እየተደመሰሰ ነው። አሸባሪውን ትህነግ ለብልቦ ለመጨረስ በቂ ኃይል ተዘጋጅቷል።
ሌላውና ወሳኙ ጉዳይ ለታጋዮቻችን ስንቅና አጠቃላይ አውደ ዉጊያውን በተሳካ ድል ለመደምደም በውጭም በሀገር ውስጥም ያሉ ወገኖቻችን በገንዘብና በስንቅ እያደረጉ ያሉት ዝግጅት በከፍተኛ ደረጃ ጨምሯል። ከፍተኛ ገንዘብ ተሰብስቧል። የተለያየ አይነት የሠራዊቱ ስንቅም ተዘጋጅቷል። እየተዘጋጀም ይገኛል። ይህንን ገንዘብና ልዩ ልዩ ሬሽኖች ለወገን ታጋዮቻችን ለሎጅስቲክስና የቀለብ ችግር እንዳይገጥመው እየተሠራ ይገኛል።
መላው ሕዝባችንም የክተት ጥሪውን ተከትሎ በከፍተኛ የማሸነፍ ወኔ የሚጠበቀውን ሁሉ እያደረገ ይገኛል።
ሕዝባችን ለህልውና ዘመቻው እያደረገው ያለው የድጋፍ ሰልፍም ውጊያውን ለመቀላቀልና አሸባሪውን ቡድን ለማሰናበት ያለውን ዝግጁነትና ጉጉት የሚያሳይ ነው።
ድል ለአማራ ህዝብ ፣ ድል ለመላ ኢትዮጵያውያን!
ሐምሌ 20/2013 ዓ.ም

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here