‹‹የዓድዋ ድል በሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት ደርምሶ ሰው ለሕግ እንዲገዛ ያደረገ ተገዳዳሪ የሌለው የድል ቀን ነው፡፡›› አቶ አብርሃም አለኸኝ

0
53

‹‹የዓድዋ ድል በሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት ደርምሶ ሰው ለሕግ እንዲገዛ ያደረገ ተገዳዳሪ የሌለው የድል ቀን ነው፡፡›› አቶ አብርሃም አለኸኝ
ባሕር ዳር: የካቲት 19/ 2013 ዓ.ም (አብመድ)125ኛው የአድዋ ድል በዓል በባሕር ዳር ከተማ እየተከበረ ነው፡፡በበዓሉ የተገኙት በምክትል ርዕሰ መስተዳድር ማዕረግ የርዕሰ መስተዳድሩ የሕዝብ ግንኙነት ተሳትፎና አደረጃጀት አማካሪ አቶ አብርሃም አለኸኝ የዓድዋ ድል ለሁሉም የተጨቆኑ ሕዝቦች ድልን ያጎናጸፈ ፤በሰዎች መካከል ያለውን ልዩነት ደርምሶ ሰው ለሕግ እንዲገዛ ያደረገ ተገዳዳሪ የሌለው የድል ቀን እንደሆነም ነው የገለጹት፡፡
‹‹ሁላችንም የኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የዓድዋ ድል ውጤት ነን፤ ያኔ ተሸንፈን ቢሆን ኖሮ ዛሬ በዚህ ደረጃና የሥነልቦና ጥንካሬ ኖሮን አንገኝም ነበር›› ብለዋል። የአባቶቻችን ተጋድሎ ባይኖር ኖሮ አሁን ባለን የስነ ልቦና ከፍታ ላይ መገኘት እንደማንችል ነው የገለጹት አቶ አብርሃም፡፡
‹‹እኛ የተፈጠርነው ለማሸነፍ እንደሆነ አባቶቻችን አሳይተውናል፤ እኛም በብሔርተኝነት፣ በጎጥ፣ ለድህነት ልንሸነፍ አይገባም›› ብለዋል። ከኢትዮጵያውያን ውጪ ኢትዮጵያ የማትታሰብ መሆኑንም ተናረዋል፡፡ አቶ አብርሃም እንዳሉት ኢትዮጵያውያን ጥቅምት 24 የተቃጣብንን የመከትነው የዓድዋ ውጤት በመሆናችን እንደሆነ ጠቅሰዋል።
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ባዬ አለባቸው የዓድዋ ድል በዓል የጣሊያንን ወራሪ ኀይል መክተው ለዚህ ቀን ያበቁን ጀግኖች ኢትዮጵያውያን የሚዘከሩበት መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ‹‹ሁሉንም ኢትዮጵያዊ በደም ላስተሳሰረው ታላቅ የድል በዓል እንኳን አደረሳችሁ›› ብለዋል፡፡
የዓድዋ ድል 125ኛው በዓልን የውይይት መድረኩን ያዘጋጁት የአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ፣ የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲና የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር በጋራ በመሆን ነው።
በውይይቱ የፌዴራልና የክልሉ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ:- ብሩክ ተሾመ

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here