የውጭ ዜጎችን ምዝገባ ማራዘሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

0
42

አዲስ አበባ: ነሐሤ 05/2014 ዓ.ም (አሚኮ) ቀደም ሲል በዓለም አቀፍ ሕግ መሰረት በኢትዮጵያ ውስጥ የሚገኙ የውጭ ዜጎች ያሉበትን ሁኔታ እና መጠን የመኖሪያ ፈቃድ የተመለከተ ምዝገባ ከሐምሌ 11/2014 ዓ.ም ጀምሮ ሲደረግ መቆየቱ ይታወሳል።

በአሁኑ ጊዜ ምዝገባው ለተጨማሪ ጊዜ መራዘሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር መለስ አለም ገልጸዋል። ቃል አቀባዩ እንዳሉት እስከአሁን ከ36 ሀገራት 70 ሺህ ዜጎች መመዝገብ የተቻለ ሲሆን በሀገር ውስጥ ይኖራሉ ተብለው ከሚገመቱት የውጭ ዜጎች አንጻር ቁጥሩ ዝቅተኛ በመሆኑ እስከ ነሐሴ 13 /2014 ዓ.ም መራዘመኑን ገልጸዋል።

የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እንዲያልቅ መንግሥት ቁርጠኝነቱን ያሳየ ሲሆን ለሰላም ድርድሩ ያለውን አቋም ኦሊሴጎን ኦባሳንጆ የሚመሩት የአፍሪካ ኀብረት ልዑክ እንዲመራ መንግሥት አሁንም አቋሙን ማጠናከሩን አምባሳደር መለስ አለም ተናግረዋል።

መንግሥት በትግራይ ክልል መሰረተ ልማቶችን መልሶ ለመገንባት ቅድመ ሁኔታ አያስቀምጥም። የመንግሥት አቋም ይህ ነው ሲሉ አብራርተዋል። በአካባቢው መሰረተ ልማቶችን ከመጠገን፣ ለማስጀመር እና ለማስኬድ ያሉትን ነባራዊ ሁኔታዎች ግን ማጤን ብቻ አስፈለጊ መሆኑን ቃል አቀባዩ አብራርተዋል።

በሌላ በኩል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮነን ከአንጎላ አቻቸው ጋር በሳምንቱ መወያየታቸውን አምባሳደር መለስ ጠቁመዋል።

ዘጋቢ:-አንዱአለም መናን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን‼
ከእኛ ጋር ስለኾኑ እናመሰግናለን‼
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/