የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ እየተሠራ መኾኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ።

0
28

መጋቢት 09/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን የበለጠ ለመሳብ መንግሥት ልዩ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ መኾኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ተናገሩ።
ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ እና ለመሳተፍ ፍላጎት ካላቸው የሕንድ ባለሀብቶች እና ከሕንድ የኢንቨስትመንት ፎረም አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።
በውይይቱ ላይ የተሳተፉ ሕንዳውያን ባለሀብቶች የውጭ ምንዛሬ አቅርቦት፣ ከፀጥታ እና ከቀረጥ ጋር የተያያዙ ጥያቄዎችን አንስተዋል ።
አምባሳደር ሬድዋን ኢትዮጵያ ካለፉት ሦስት የለውጥ ዓመታት ወዲህ ከአሁን በፊት ለውጭ ባለሀብቶች ክፍት ያልኾኑ የኢንቨስትመንት ዘርፎችን ጭምር ክፍት ማድረጓን አስታውሰዋል።
የሕንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በአስቸጋሪ ወቅትም መዋለ ንዋያቸውን በማፍሰስ ሌሎች ባለሀብቶች ወደ ኢትዮጵያ እንዲመጡ መልካም አብነት ያላቸው ናቸው ብለዋል።
ከባለሀብቶቹ ለተነሱት ጥያቄዎች ልዩ ትኩረት በመስጠት እንደ ሀገር ለኹሉም ባለሀብቶች ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታ እንዲፈጠር ይሠራል ማለታቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ጽሕፈት ቤት የተገኘ መረጃ ያመላክታል።
የሕንድ ባለሀብቶች ኢትዮጵያ በዘርፉ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን በፍጥነት መፍታት ከቻለች በአፍሪካ ቀንድ ብቻ ሳይኾን በአፍሪካ አህጉር ትልቋ የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንት መዳረሻ የመኾን አቅም እንዳላት ተናግረዋል።
የኢትዮጵያ መንግሥት ከባለሀብቶች የሚነሱ ጥያቄዎችን ጊዜ ሰጥቶ በማዳመጥ ለክፍተቶች እልባት ለመስጠት ያለውን ቁርጠኝነት ከውይይቱ በመረዳታችን ደስተኞች ነን ብለዋል።
አሁን ላይ ከ600 በላይ የሕንድ ባለሀብቶች በኢትዮጵያ በተለያዩ የኢንቨስትመንት ዘርፎች ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ።
#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J
በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/