የወልድያ ሰላም ተጠብቆ እንዲዘልቅ የከተማዋ ወጣቶች እያደረጉት ያለውን ተጋድሎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን ጠየቁ።

0
112

የወልድያ ሰላም ተጠብቆ እንዲዘልቅ የከተማዋ ወጣቶች እያደረጉት ያለውን ተጋድሎ አጠናክረው እንዲቀጥሉ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን ጠየቁ።

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 30/2013 ዓ.ም (አሚኮ)የወልድያ ከተማ በሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ እንደምትገኝ የከተማዋ ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን አስታውቀዋል።

የወልድያ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ያሲን እንዳሉት ተስፋፊውና ሰው በላው አሸባሪው የትህነግ ቡድን በእጅጉ ከሚመኛት ከተማ አንደኛዋ ናት። በወልድያና አካባቢው የሚገኙ ወጣቶች ከመቼውም ጊዜ በላይ ራሳቸውን አደራጅተው እና አንቅተው ከከተማ አስተዳደሩ፣ ከዞኑ አስተዳደርና ከጸጥታ ተቋሙ ጋር በቅንጅት አካባቢን የመጠበቅ ሥራ እየሠሩ ነው ብለዋል።

የከተማዋ ቁልፍ የሚባሉ በሮችና ለጥቃት ያጋልጣሉ የሚባሉ ተራራዎችን በንቃት የመጠበቅ ሥራ እየተሠራ መሆኑንም ገልጸዋል። ወደ ከተማዋ የሚቃጡ የትኛውንም አደጋ በመከላከል እና ተላለኪዎችን በመቆጣጠር ላይ መሆናቸውንም ገልጸዋል።

ከተማዋ እንደወትሮው ሁሉ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ላይ ናት ያሉት ከንቲባው የጠላት ኀይል ወልድያን እንደተቆጣጠረ አድርጎ የሚያናፍሰው ወሬ ውሸት ነው፤ ከከተማዋ ነዋሪዎች የበለጠ አስረጅ የለም ነው ያሉት።

የከተማዋ ወጣቶችና ነዋሪዎች ጠላት የሚገባበትን ቀዳዳ በመድፈን እያሳዩት ያለውን ጥንካሬ አጠናክረው እንዲቀጥሉም ጠይቀዋል። የከተማዋ ነዋሪዎች ሳይደናገጡ የየዕለት ሕይወታቸውን እንዲቀጥሉም አስገንዝበዋል።

የአሚኮ የጋዜጠኖች ቡድንም በወልድያ ከተማ ባደረገው ቅኝት ወጣቶች አካባቢያቸውን በንቃት እየጠበቁ መሆኑን አረጋግጧል።

ዘጋቢ:- ታርቆ ክንዴ – ከወልድያ

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4

LEAVE A REPLY

Please enter your comment!
Please enter your name here