የኢኮኖሚ አሻጥሩን ለመቆጣጠር ኅብረተሰቡ እገዛ እንዲያደርግ የሰሜን ሸዋ ዞን ጠየቀ፡፡

0
106

ደብረ ብርሃን: የካቲት 30/2014 ዓ.ም (አሚኮ) በዘይት ምርት ላይ የሚታየውን የዋጋ ንረት ለማረጋጋት እየሠራ መሆኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ አስታውቋል፡፡

ዞኑ 754 ሺህ ሊትር የድጎማ ዘይት በአንባሰል የንግድ ሥራዎች ድርጅት በኩል ማቅረቡን የሰሜን ሸዋ ዞን ንግድና ገበያ ልማት መምሪያ ኀላፊ ኀይሌ ዳኛቸው ገልጸዋል፡፡

አቶ ኀይሌ እንዳሉት እንደ ሀገር የተፈጠረውን የኢኮኖሚ አሻጥር ለመቆጣጠር ግብረ ኀይል ተቋቁሞ እየሠራ ነው፡፡

በባለፉት 2 ቀናት ብቻ በተደረገ ቁጥጥር 604 ሕገወጥ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ መወሰዱን እና በሌሎች 4 ነጋዴዎች ላይ ክስ መመስረቱንም ኀላፊው አስረድተዋል፡፡

ቁጥጥሩ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያብራሩት ኀላፊው ሕዝቡም ሕገወጥ ነጋዴዎችን በማጋለጥ ኀላፊነቱን እንዲወጣ ጠይቀዋል፡፡

ዘጋቢ፡-ገንዘብ ታደሰ-ከደብረ ብርሃን

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ ‼️
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ‼️
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ‼️
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ‼️

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/336LQaS
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በሰቆጣ፣ ቆቦ፣ ወልድያ፣ ላልይበላ፣ ደሴ እና ከሚሴ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/