የኢንዱስትሪ ሚኒስተሩ አቶ መላኩ አለበል በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የተዘጋጀውን የፋሽን ኤግዚቢሽንና ባዛር ጎበኙ።

10

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 18/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ተቋሙ በ11ኛው ዓለም አቀፍ የ”ጥጥ፣ ቴክስታይል እና የአልባሳት እሴት ሰንሰለት በአፍሪካ” ኮንፈረንስ ያዘጋጀውን የኢግዚብሽን ባዛር አስጎብኝቷል።

በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት በ11ኛው ዓለም አቀፍ የ “ጥጥ፣ ቴክስታይል እና የአልባሳት እሴት ሰንሰለት በአፍሪካ” እና በ1ኛው ሀገር አቀፍ ዩኒቨርሲቲ ኢንዱስትሪ ትስስር ፎረም ላይ በክብር እንግድነት የተገኙት አቶ መላኩ አለበል የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ሚኒስተር አምባሳደር የሽመብራት መርሻ (ዶ/ር) እና ፍሬው ተገኘ (ዶ/ር)

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት እንዲሁም ዶክተር ታምራት ተስፋዬ በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ሳይንቲፊክ ዳይሬክተር የኢግዚቢሽን ባዛሩን መርቀው ከፍተዋል::
በኢግዚቢሽን ባዛሩ ጉብኝት ወቅት የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ባለፉት 60 ዓመታት ዩኒቨርሲቲው ከሠራቸው ትልልቅ ሥራዎች መካከል ለሀገር ግንባታ ከፍተኛ አስተዋፅኦ የሚያደርጉ ተመራማሪዎችን መምህራንን እና ሙሁራንን ሲያፈራ በዚህ የሀገር ግንባታ ተሳትፎ ድግሞ የኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጅ ኢንስቲትዩት ከፍተኛ ሚና ከነበራቸው የትምህርት ዘርፍፎች አንዱ ተብሏል::

የኢንስቲትዩቱ መረጃ እንደሚያሳየው፤ በባዛሩ ተሳታፊ የሆኑት የኢንስቲትዩቱ የቀድሞ ተማሪዎችና በግል ሥራ በመስማራት ራሳቸውን የኢኮኖሚ ባለቤት ያደረጉ እና በቴክስታይልና ጋርመንት እንዲሁም በቆዳና ቆዳ ውጤቶች ላይ የተሰማሩ አካላት ሲሆኑ ከእዲስ አበባ ከባሕር ዳር ከኮምቦልቻ ከአዳማና ከሌሎች የኢንዱስትሪ መንደር የመጡ ተሳታፊዎች ናቸው።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!