የኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር፣ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ ለአማራ ክልል 14 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረጉ፡፡

261

ባሕር ዳር፡ ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) አሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን በወረራ ይዟቸው በነበሩት የአማራ ክልል አካባቢዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋምና የወደሙ ተቋማትን ለመገንባት የፌዴራል ሚኒስትር መሥሪያ ቤቶች የተለያዩ ድጋፎችን እያደረጉ ነው።

የኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር፣ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ በአሸባሪው የትግራይ ወራሪ ቡድን የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም እና የወደሙ ተቋማትን መልሶ ለመገንባት የሚውል 14 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

የኢንዱሰትሪ ሚኒስቴር፣ ንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና ተጠሪ ተቋማቱ የኢትዮጵያ ንግድ ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት፣ የኢትዮጵያ ሲሚንቶ አከፋፋዮች ማኅበር ጋር በመሆን 10 ሚሊዮን ብር በጥሬ ገንዘብና 4 ሚሊዮን ብር በዓይነት አስረክበዋል።

ድጋፉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል አስረክበዋል፡፡

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ። https://ameco.bankofabyssinia.com/