የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የሚጀመርበት ቀን ታወቀ፡፡

759
ባሕር ዳር፡ መስከረም 26/2013ዓ.ም (አብመድ) በ2012ዓ.ም በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት የተሰረዘው የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ የ2013ዓ.ም የውድደር ዘመን የሚጀምርበት ቀን ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ፕሪሚዬር ሊግ ሸር ካምፓኒ በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ውስጥ ሆኖ የ2013 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር ለማስጀመር ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን የቅደመ ዝግጅት ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል ተብሏል፡፡
ከኢትዮጵያ ስፖርት ኮሚሽን የተገኜው መረጃ እንደሚያመላክተው ዝግጅቱን መሠረት በማድረግ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሩ ታኅሣስ 03 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚጀመር ለተሳታፊ ቡድኖች አሳውቋል፡፡ ቡድኖችም የውድድሩን ቀን በማወቅ ከወዲሁ ዝግጅት እንዲያደርጉ አሳስቧል፡፡
ተጨማሪ መረጃዎችን ከአብመድ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ