የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ለተፈናቃይ ወገኖች 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የምግብ ድጋፍ አደረገች፡፡

0
53

ባሕር ዳር፡ ጥር 06/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በሽብርተኛው የትግራይ ወራሪ ቡድን ወረራ ምክንያት ተፈናቅለው በደባርቅ ከተማ መጠለያ ጣቢያ ለሚገኙ ወገኖች 2 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የፊኖ ዱቄት ድጋፍ አድርጋለች፡፡

የስዊድን እና አካባቢው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልያስ፣ የሰሜን ጎንደር ዞን እና የጅማ ዞን አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ እስጢፋኖስ እና ሌሎች አባቶች ደባርቅ ከተማ በሚገኘው የተፈናቃዮች መጠለያ ጣቢያ ተገኝተው ድጋፉን አስረክበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን በአማራ ክልል በኹሉም አካባቢዎች በወራሪው ቡድን ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፍ ስታደርግ መቆየቷን ጳጳሳቱ አንስተው ወደፊትም የተጎዱ ወገኖችን መደገፏን አጠናክራ እንደምትቀጥል አረጋግጠዋል፡፡

የሰሜን ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ያለዓለም ፈንታሁን እና የዞኑ የአደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አቶ ሰላምይሁን ሙላት ድጋፉን ተረክበዋል፡፡

ዘጋቢ፡-አድኖ ማርቆስ-ከደባርቅ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ tiktok.com @amharamediacorporation

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/