የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዳቦ ዱቄት ለተጎጂዎች ድጋፍ አደረገ።

0
107

ደብረ ብርሃን፡ ጥር 26/2014 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዳቦ ዱቄት በሰሜን ሸዋ ዞን በተለያየ ምክንያት በችግር ላይ ለሚገኙ ወገኖች ድጋፍ አድርጓል።

ቅዱስ ሲኖዶስ ጥቅምት ወር ላይ ባሳለፈው ውሳኔ መሠረት
በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች የተጎዱትን በማሠብ ለጊዜው የሚሆን የመጀመሪያ ዙር ድጋፍ የተደረገ መሆኑን ድጋፉን ያስረከቡት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን የመተከልና አዊ ዞን ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ቶማስ ገልጸዋል።

ድጋፉን የተረከቡት የሰሜን ሸዋ ዞን አስተዳደር ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ እንግዳሸት በጋሻዉ በቤተክርስቲያኗ ለተደረገዉ ድጋፍ አመስግነዉ ድጋፉ ለተጎጅዎች በአግባቡ እንደሚደርስ ተናግረዋል።

ዘጋቢ:–ብርቱካን ማሞ

#ኢትዮጵያን እናልማ፣እንገንባ፣እንዘጋጅ!
#ሀገርን በዘላቂነት እናልማ!
#የፈረሰውን አብልጠን እንገንባ!
#ለማንኛውም ፈተና እንዘጋጅ!

ተጨማሪ መረጃዎችን ከአሚኮ የተለያዩ የመረጃ መረቦች ቀጣዮቹን ሊንኮች በመጫን ማግኘት ትችላላችሁ፡፡
ዩቱዩብ https://bit.ly/2RnNHCq
በዌብሳይት amharaweb.com
በቴሌግራም https://bit.ly/2wdQpiZ
ትዊተር https://bit.ly/37m6a4m
ቲክቶክ https://bit.ly/32rKF5J

በአሸባሪውና ወራሪው የትግራይ ቡድን በዋግኽምራና በወሎ አካባቢዎች የወደሙና የተዘረፉ የሚዲያ መሳሪያዎችን መልሶ በመገንባት ለሕዝብ አገልግሎት ለመስጠት አሚኮን ይደግፉ።
https://ameco.bankofabyssinia.com/