የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን ረቡዕ ይጀምራል።

53
ባሕርዳር: መጋቢት 04/2015 ዓ.ም (አሚኮ) በአይቮሪኮስት አስተናጋጅነት ለሚከናወነው የ2023 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣርያ ጨዋታዎች በማድረግ ላይ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የምድቡን ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎች ከጊኒ አቻው ጋር በሞሮኮ ራባት መጋቢት 15 እና 18 ያከናውናል።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ ማድረጋቸው የሚታወስ ነዉ ። የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እንዳስታወቀው የብሔራዊ ቡድኑ አባላት ረቡዕ መጋቢት 6 በመሰባበስ ዝግጅታቸውን የሚጀምሩ ይሆናል።
ኢትዮጵያ በማጣርያው ምድብ አራት ከግብፅ ፣ ማላዊ እና ጊኒ ጋር ተደልድላ በመወዳደር ላይ ስትሆን ከሁለት ጨዋታ 3 ነጥብ እና 1 የግብ ልዩነት በመያዝ ምድቡን በመምራት ላይ ትገኛለች።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!